
ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር) ለአገው ፈረሰኞች በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የተከበርከው ሕዝባችን በፍፁም ሀገር ወዳድነት መንፈስ እና የአርበኝነት ወኔ ዋጋ የከፈልክበት፣ ይህንኑ ለመዘከር እና ለማስታወስ፣ ባሕልና ቅርሱን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታስቦ ለተቋቋመው 85ኛው የአገው ፈረሰኞች ክበረ በዓል በሠላም አደረሣችሁ አደረሠን እላለሁ” ነው ያሉት።
ይህ ታላቅ ክብረ በዓልም የሕዝባችንን ዕሴት፣ ባሕልና ወግ ጠብቆ እንዲዘልቅ የሚያደርግ ነው ያሉት ኀላፊው በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በጉልህ እንዲታወቅና ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው ጋር የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን የምንቀጥል መኾኑን ስገልፅ በታላቅ ደስታና ኩራት ጭምር ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!