
ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አመታት የተሠሩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተሠሩት የአዲስ አፍሪካ ኤግዚቢሽንና ኮንቬሽን ማዕከል እና የተለያዩ ማዕከላት ግንባታ የሚደነቅ ሆኖ መመልከታቸውን በመርሐ ግበሩ እየተሳተፉ የሚገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ስኬት የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ቁርጠኝነትን የተመለከቱበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ዘመናዊ የንግድ ስርዓትን ለመፍጠር በከተማዋ የተገነቡ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላትን ጨምሮ እየተካሄዱ ያሉ የግብርና ሥራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸውም ብለዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎር እንደዘገበው በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበሩ የሚገኙ የተለያዩ ልምዶችን በመውሰድ ክልላቸውን ለማልማት እየሠሩ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!