
ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
በግምገማው የአማራ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢዎች ተገኝተዋል።
የአማራ ክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቤል ፈለቀ ባለፉት ስድስት ወራት መሠረተ ልማትን በመገንባት፣ ዲጂታላይዜሽን እና ኦቶሚሽንን በማስረጽ፣ ተቋማዊ መስተጋብር እና ትስስር በመፍጠር ረገድ አበረታች ሥራዎችን ማከናዎን ተችሏል ብለዋል።
በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከዞኖች ጋር የተሟላ መረጃ መለዋወጥ እና ወደ ታችኛው እርከን ተንቀሳቅሶ ለመሥራት አስቸጋሪ እንደነበር አንስተዋል።
ባለፈው ተመሳሳይ ዓመት የኮሚሽኑ አፈጻጸም 36 በመቶ የነበረ ሲኾን ዘንድሮ በችግር ውስጥ ኾኖም 72 በመቶ ፈጽሟል ነው የተባለው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!