
ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡
የረቂቁን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ.ር) አቅርበዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ትምህርትን በእኩልነት እና ፍትሐዊነት በመላ ሀገሪቷ ተደራሽ ለማድረግ የጎላ ሚና እንዳለው ሰብሳቢው አብራርተዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የመምህራንን ጥራት እና ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና የትምህርት አሥተዳደሩን ብቃት ለማረጋገጥ ድርሻው ከፍተኛ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡
የአስተማሪነት ሙያ እንዲከበር እና በሂደትም የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ለመስጠት ረቂቅ አዋጁ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1368/2017 ኾኖ በሁለት ተቃውሞ፣ በአሥር ድምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!