
አዲስ አበባ: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የሚሳተፉ የፓርቲው አባላት እና ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
የጉብኝቱ አካል ከኾኑ ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ መሬት እና አሥተዳደር ቢሮ የለወጥ ተግባራት፤ የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እና የለሚ እንጀራ ፋብሪካ ማዕከል ይገኙበታል።
ጉብኝዎች በተመለከቱት የለወጥ ሥራ መደነቃቸውን ተናግረዋል። ይህ ተግባር በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በስፋት ሊተገበር ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!