
ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሂደ ነው። ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው አቶ ብርሃኑ አዴሎ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል።
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ለሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር በመኾን የተሾሙት አቶ ብርሃኑ በጉባዔው ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!