የአገው ፈረሰኞች በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ አስፈላጊው መረጃ ተጠናቅቋል።

32

ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ ሁነቶች እየደመቀ የሚከበረውን የአገው ፈረሰኞች በዓል በዩኒስኮ ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ መረጃዎች በሙሉ ተጠናቅቀው ለሚመለከታቸው አካላት ገቢ መደረጉን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዓሉን የተመለከቱ በርካታ ጥናቶችን ማካሄዱንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። በዩኔስኮ ለምዝገባ የሚፈልጋቸውን ሙሉ መስፈርቶች የሚያሟላ ቅጽ ተሞልቶ መላኩንም አንስተዋል።

የቅርሱ የምዝገባ ሂደት ምን እንደሚመስል እየተከታተሉ መኾኑንም ገልጸዋል። የምዝገባ ሂደቱን እየጠበቀ መኾኑን ተነግሮናል ነው ያሉት።

“አስፈላጊው መረጃ ከተላከ በኃላ ‘ወረፋ ጠብቁ’ መባሉ የተቀናጀ ክትትል አለመኖሩን ይጠቁማል ያሉት ፕሬዝዳንቱ በዓሉ በቅርቡ እንዲመዘገብ ከክልል እስከ ፌዴራል መንግሥት የተቀናጀ የክትትል ሥራ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ብልጽግና ሰው ተኮር ፓርቲ ነው” አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር
Next articleአቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።