“ብልጽግና ሰው ተኮር ፓርቲ ነው” አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር

94

ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች እና አባላት በአዲስ አበባ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው። በጉብኝቱ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ብልጽግና ፓርቲ ቃል ከገባቸው ጉዳዮች መካከል ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት እየተገበረ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ የተገነቡና የሚገነቡ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ሥራዎችም ለመዲናዋ ነዋሪዎች እና ጎብኝዎች ምቹ ከባቢን በመፍጠር ሰው ተኮር ሥራዎች በተግባር የተገለጡባቸው መኾናቸውን ገልጸዋል። የፒያሳና አካባቢው፣ አራት ኪሎ አካባቢ የተገነቡ እና የሚገነቡ የመሠረተ ልማት ሥራዎች በሀገራችን እንዲኾኑ ስንመኛቸው የነበሩ ናቸው ብለዋል።

ብልጽግና ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ያሉት አፈጉባኤው በመዲናዋ የሚገነቡ መሠረተ ልማቶችም ለሁሉም ዜጎች ምቹ ሁኔታን መፍጠር የቻሉ መኾናቸውን ገልጸዋል። ሁለተኛው የፓርቲው ጉባኤም የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል ሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉበት ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት አስታውቀዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በመዲናዋ በጥራትና በፍጥነት የተገነቡ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችም ለክልል ከተሞች ትምህርት የሚሰጡ እና እየተሠራባቸው የሚገኙ መኾናቸውን ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ መካሄድ ይጀምራል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕግ ማስከበር ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ነው።
Next articleየአገው ፈረሰኞች በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ አስፈላጊው መረጃ ተጠናቅቋል።