የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ የአንድነት ፓርክን ጎበኙ።

23

ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡት የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ዌለርስ ጋሳማጌራ የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።

ጋሳማጌራ በፈረንጆቹ 1987 የተመሠረተውን የሩዋንዳ ፓትሪዮቲክ ፍሮንት (አር ፒ ኤፍ) በዋና ፀሐፊነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ቀደም ሲል በአንጎላ የሩዋንዳ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ጉባዔው በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአዲሱ ክስተት “ዲፕሲክ”
Next articleየ”ጥርን በባሕርዳር” አንድ አካል የኾነው የባሕል አውደርዕይ እየተካሄደ ነው።