
ባሕር ዳር : ጥር 22/2017 ዓ.ም(አሚኮ) ከጥር 23 አስከ 25 በሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የሚሳተፉ የፓርቲው ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ እና በመገንባት ላይ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።
አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የሚያዘምኑ የመሠረተ ልማት አውታሮችን እና የኑሮ ውድነቱን የሚያቃልሉ ፕሮጀክቶችን መመልከታቸውን ጎብኚዎቹ ተናግረዋል።
“ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት በሚካሄደው የፓርቲው መደበኛ ጉባኤ ላይ 1ሺህ 700 በድምጽ የሚሳተፉ የፓርቲው መሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች እና የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እንደሚሳተፉ ኢቢሲ ዘግቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
