በእስቴ ወረዳ ሕዝባዊ የሰላም ውይይት ተካሄደ።

17

ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ በዝጎራ፣ ደንጎልትና መካነ ኢየሱስ ቀበሌ ሕዝባዊ የሰላም ውይይት ተካሂዷል።

በሕዝባዊ ውይይቱ ስለ ሰላም፣ ልማትና መልካም አሥተዳደር በስፋት ተነስቷል። እየገጠመ ያለውን የሰላም ችግር ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የእስቴ ወረዳ አሥተዳዳሪ ማንተፋርዶ ሞላ ሰላምን ማምጣት የሚችለው ራሱ ሕዝቡ ነው ብለዋል። ከደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ለሰላም ሁላችንም የየድርሻችን እንወጣ ነው ያሉት። ሰላምን እንስበክ ለሰላምም እንሥራ ብለዋል ዋና አሥተዳደሪው በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰሜን ጎጃም ዞን የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራን በይልማና ዴንሳ ወረዳ አስጀመረ።
Next articleየኮምቦልቻ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል።