የተፈጥሮ ሀብትን እንደ ልጅ መንከባከብ ይገባል።

30

ሰቆጣ: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ትምህርት ቤቶች የእውቀት ምንጭ ከመኾናቸውም ባሻገር ተማሪዎች የተፈጥሮ ፀጋዎችን ለይተው እንዲያውቁ እና እንዲመራመሩ የሚያደርጉ የምርምር ተቋማት ናቸው። ስለ ተፈጥሮ ሀብት ጠቀሜታም በአካባቢ ሳይንስ ትምህርት እንዲማማሩ ይደረጋል።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ድሃና ወረዳ ሲልዳ ቀበሌ በተጀመረው የተፈጥሮ ሀብት የማስጠበቂያ መርሐ ግብር በመገኘት የልማቱ አጋር መኾናቸውን አሳይተዋል።

የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ ለተተኪው ትውልድ የተሻለ ሀገርን ማስረከብ የወላጆች ግዴታ መኾኑን ተማሪዎቹ ተናግረዋል። ወላጆችም ለልጆቻቸው የሚያስፈልገውን ነገር እንደሚያደርጉ ሁሉ የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ እራሳቸውም ተተኪ ልጆችም ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማድረግ ይገባቸዋል ነው ያሉት ተማሪዎቹ።

የሲልዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአካባቢ ሳይንስ መምህሩ ሙላት ወዳጅ ልጆች የተፈጥሮ ሀብትን ጠቀሜታ እንዲረዱ በቃል ከማስተማር ባሻገር በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ በተግባርም ጭምር እያሳዩ መኾኑን ጠቅሰዋል።

ወላጆችም የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ለሀገርም፣ ለራሳቸውም እንደሚጠቅም በመረዳት ለመንግሥት ብለው ሳይኾን ለራሳችን በሚል ስሜት እንዲያለሙ አሳስበዋል የሳይንስ መምህሩ።

በጥያ ተፋሰስ በተጀመረው የተፈጥሮ ሀብት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ተማሪዎች መሳተፋቸው ለወላጆች ትልቅ መነሣሣት ይፈጥራል ያሉት ደግሞ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኀላፊ አዲሱ ወልዴ ናቸው።

ተማሪዎቹም” የተራቆተ መሬት አንረከብም፣ ለዋግ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ያስፈልጋታ” የሚሉ እና ሌሎች መፎክሮችን በመያዝ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃው ለተገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ:- ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleእስቴ መካነኢየሱስ ለመርቆሪዎስ በዓል ተሞሽራለች።
Next articleሰሜን ጎጃም ዞን የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራን በይልማና ዴንሳ ወረዳ አስጀመረ።