
ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአልጄሪያ ብሔራዊ ነፃነት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር አብደልከሪም ቤን መባረክ የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሐሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሂዳል።
በጉባኤ ላይ የሚታደሙ የውጭ ሀገራት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
የአልጄሪያ ብሔራዊ ነፃነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ፕሮፌሰር አብደልከሪም ቤን መባረክ በጉባኤው ለመታደም ሌሊት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ኢዜአ እንደዘገበው የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!