
ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተርክዬ ኤኬ ፓርቲ እና የሞሮኮው ናሽናል ራሊ ኦፍ ኢንዲፔንደንትስ(አር ኤን አይ) ፓርቲ አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ።
ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ” ከቃል እስከ ባሕል ” በሚል መሪ ሀሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሂዳል።
በጉባዔው ላይ የሚታደሙ የውጭ ሀገራት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
በዚህም የተርክዬው ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዛፈር ሲራካያ እና የሞሮኮው ‘ናሽናል ራሊ ኢንዲፔንደንትስ’ (አር ኤን አይ) ፖርቲ ተወካይ መሐመድ ሳዲኪ ዛሬ ዕኩለ ሌሊት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ኢዜአ እንደዘገበው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ.ር)፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለእንግዶቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!