በምዕራብ ጎጃም ዞን በስምንት ወረዳዎች የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ እየተከናወነ ነው።

43

ፍኖተ ሰላም: ጥር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ የሚሠራው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና ልማት ሥራ ለቀጣይ ትውልድ ወሳኝ በመኾኑ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል በሥራው እንዲሳተፍ የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ አሳስቧል።

የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ የተጎሳቆሉ ተፋሰሶችን መልሶ በማልማት የእርሻ መሬትን በጎርፍ እንዳይጋለጥ እና ለምነቱ እንዲጨምር ዓይነተኛ ሚና አለው።

በምዕራብ ጎጃም ዞን በስምንት ወረዳዎች የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

የተፈጥሮ ሃብት እና ጥበቃ ሥራው በ106 ተፋሰሶች ላይ 23 ሺህ 523 የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ መኾናቸውን የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተስፋዬ አስማረ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ የህልውና ጉዳይ በመኾኑ አርሶ አደሩ በችግርም ውስጥ ኾኖ ሥራውን እያከናወነ መኾኑን ኀላፊው ገልጸዋል።

አካባቢውን ከመጠበቅ እና ከማልማት ባሻገር አርሶ አደሮች በእንስሳት ርባታ፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ ሥራ ላይ ውጤታማ መኾናቸውን ነው ያነሱት።

ዛሬ የሚሠራው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና ልማት ሥራ ለቀጣይ ትውልድ ወሳኝ በመኾኑ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል በሥራው እንዲሳተፍ ነው ኀላፊው ያሳሰቡት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለስምንት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የዳልጋ ከብቶች ክትባት ዘመቻ ተጀመረ።
Next articleየሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ ገብተዋል።