
አዲስ አበባ: ጥር 21/2017 ዓ.ም(አሚኮ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የገንዘብ ተቋማት ባለሙያዎች የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ስቱዲዮን ጎብኝተዋል።
አሚኮ በአዲስ አበባ ያስገነባውን አዲስ ዘመናዊ ስቱዲዮን የጎበኙት የገንዘብ ተቋማት ባለሙያዎች ሕዝብ እና ሀገርን ለማገልገል ዘመናዊ መሣሪያዎችን አሟልቶ ያስገነባው ስቱድዮ ቀዳሚ እና ተመራጭ እንዲኾን ያደርገዋል ብለዋል።
አሚኮ ባለው የፕሮግራም አካታችነት እና የዘገባ ጥራት ምክንያት የብዙ ተቋማት የሚዲያ አጋር ሆኖ መቆየቱን የተናገሩት የገንዘብ ተቋማት ባለሙያዎቹ አዲሱ ስቱዲዮ ተቋማት ከሚዲያው ጋር አብሮ ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት ይበልጥ ከፍ የሚያደርግ እንደኾነ ተናግረዋል።
በቀጣይም ኮርፖሬሽኑ ያሉትን ጥንካሬዎች አስቀጥሎ እንድሄድም ባለሙያዎቹ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ: ቤቴል መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን