የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

53

ባሕር ዳር: ጥር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በ17ኛ መደበኛ ስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያጸድቃል ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል ርብርብ ይጠይቃል።
Next articleጥበብ የሚቀዳባት፣ ታሪክ የመላባት- ዋሸራ