“ብልጽግና ፓርቲ እየገነባው ያለው ኅብረ ብሔራዊ፣ የጋራ እና የወል ትርክት ለነገም ስንቅ የሚኾን ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ

69

ባሕር ዳር: ጥር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ፓርቲው ባለፉት ዓመታት በሠራቸው እና እየሠራቸው ባሉ ሥራዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ብልጽግና ፓርቲ ኅብረ ብሔራዊ፣ የጋራ እና የወል ትርክት በመገንባት ረገድ ትልቅ ሥራ ሠርቷል ነው ያሉት።

ፓርቲው እየገነባው ያለው ኅብረ ብሔራዊ፣ የጋራ እና የወል ትርክት ለነገም ስንቅ የሚኾን ነው ብለዋል። ኅብረ ብሔራዊ፣ የጋራ እና የወል ትርክቶች በትክክልም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የሚጥቅሙ ናቸው ነው ያሉት።

አንድነት፣ አብሮነት እና ኅብረ ብሔራዊነት ፍሬ እያፈሩ መኾናቸውንም አንስተዋል። ፓርቲው እየሠራው ያለው ሥራ ለሀገር እና ለሕዝብ የሚጠቅም መኾኑን ነው ያመላከቱት።

ብልጽግና ፓርቲ የሀገርን አንድነት ለማጽናት የጋራ እና የወል ትርክቶች ላይ በትኩረት እንደሚሠራ በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማርያም አዳራሽ – መርጡለ ማርያም !
Next articleየአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች በገቢ ላይ ለውጥ አምጥተዋል።