
አዲስ አበባ: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች አዲስ አበባ አራት ኪሎ የሚገኘውን የአሚኮ አዲሱን ስቱዲዮ ጎብኝተዋል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ለአድማጭ ተመልካች ተደራሽ በማድረግ ሀገራዊ ኀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
ተቋሙ የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት ተወዳዳሪ፣ ተመራጭ እና ቀዳሚ የሚዲያ ተቋም ለመኾንም ከክልሉ አልፎ በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፉን ከፍቶ እየሠራ ነው። በመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ የኾኑት ፍሬሕይዎት ብርሃኑ እና ምንባለ ሞላ አሚኮ በርካታ ፈተናዎችን በመቋቋም የሕዝብን አንድነት እና አብሮነት በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት አድርጎ በመዘገብ ሀገራዊ ሚናውን እየተወጣ ያለ ተቋም ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የክልል ጉዳዮች ምክትል ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አክሊሉ አሚኮ በክልሉ ብሎም በሀገር ደረጃ ሰላም እንዲሰፍን እና ልማት እንዲረጋገጥ እየተጋ ያለ የሚዲያ ተቋም ስለመኾኑ ገልጸዋል። አሚኮ ሀገራዊ፣ አሕጉራዊ እና ዓለማቀፋዊ ኹነቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች የዘገባ ሽፋን በመስጠት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ እያበረከተው ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መኾኑንም ባለሙያዎቹ አንስተዋል።
በቀጣይም የጥራት እና የተደራሽነት አድማሱን ከማስፋት ባሻገር ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር እያደረገ ያለውን የትብብር እና የቅንጅት ሥራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!