አሚኮ ምቹ ባልኾኑ ሁኔታዎች ውስጥ እያለፈ ውጤታማ ሥራን እየሠራ ያለ አንጋፋ ተቋም መኾኑን የሚዲያ ባለሙያዎች ተናገሩ።

48

አዲስ አበባ፡ ጥር 20/2017 ዓ.ም(አሚኮ) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ኀላፊዎች የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ስቱዲዮን ጎብኝተዋል።

አሚኮ በአዲስ አበባ ያስገነባውን አዲስ ዘመናዊ ስቱዲዮ የጎበኙት ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ኀላፊዎች አሚኮ በብዙ ውጣውረዶች ተፈትኖ ያለፈ በየጊዜውም ራሱን በማዘመን ተወዳዳሪ እና ተደራሽነቱን እያሰፋ የሚገኝ ታላቅ ሚዲያ ነው ብለዋል።

አሚኮ ባለፉት 30 ዓመታት በመጣበት ጉዞ የአማራን ሕዝብም ኾነ የመላው ኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ ሀገራዊ አንድነት እና አብሮነትን በማጠንከር ረገድ የሠራው ሥራ ታላቅ ምሥጋና እና ክብር የሚያሰጠው መኾኑን ተናግረዋል።

ባለፉት 30 ዓመታት የሕዝብ አብሮነት፣ ልማት እና ዕድገት ላይ የሠራው አሚኮ ራሱን በቴክኖሎጂ እና በብቁ የሰው ኅይል በመገንባት ተደራሽነቱን እያሳደገ መጥቷል ነው ያሉት። አሁን ካለበት የበለጠ ማደግ እንዳለበትም አንስተዋል።

እንደ ሀገር ለግጭት መንስኤ የኾኑ ችግሮችን በማስቀረት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር እና አብሮነትን በማጠናከር በኩል እየሠራ ያለውን ሥራ ማጠናከር እንዳለበትም ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ያስገነባው አዲስ ስቱዲዮ ከሀገር ውስጥ አልፎ ዓለም አቀፍ ተደራሽነቱን እና ተወዳዳሪነቱን ከፍ ለማድረግ ዕድል የሚፈጥር እንደኾነም ገልጸዋል።

ሚዲያው አሁን የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል የሕዝቦችን አንድነት በማጎልበት ሀገር ከገባችበት ችግር የምትወጣበትን አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦችን ማቅረብ እንደሚገባውም አመላክተዋል።

አብሮነትን የሚያጠናክሩ የጋራ እሴቶች እንዲዳብሩ፣ ፈጣን እና ተዓማኒ መረጃን ለሕዝቡ ማድረስ ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራቱ የበለጠ ተወዳዳሪ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ50 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ አስታወቀ።
Next article“አሚኮ በሀገር ደረጃ ሰላም እንዲሰፍን እና ልማት እንዲረጋገጥ እየተጋ ያለ የሚዲያ ተቋም ነው” የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች