
አዲስ አበባ: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ሰላሳ ዓመታት መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮች ለማኅበረሰቡ ሲያደርስ የቆየው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጊዜው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ብቁ የሰው ኀይልን በመገንባት ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
ሚዲያው አሁን ላይ ደግሞ በአዲስ አበባ ዘመናዊ ስቱዲዮ ገንብቶ አጠናቋል፡፡ ስቱዲዮውን የጎበኙት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን እና ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሚዲያ ባለሙያዎች አሚኮ ብዝኀነትን የሚያሳይ ተደራሽነቱን በማስፋት ቀዳሚ አማራጭ የሚዲያ ተቋም ኾኖ መገንባቱ የእድገቱ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡
ተቋሙ ከአንድ ክልል ሚዲያ እሳቤ ወጥቶ በሠራቸው ሥራዎችም እንደሃገር ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ ጉልህ አበርክቶ አለው ያሉት ባለሙያዎቹ ለማኅበረሰብ በማገልገል ረገድም ለሌሎች አርዓያ የሚኾን ተቋም መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተደራሽነቱን ከማስፋት ባሻገር ተቋማዊ አቅሙን በማሳደግ በቀጣይ የክልሉን ሕዝብ እሴት የሚያጎሉ የአቀራረብ ለውጦች ላይ በትኩረት እንዲሠራም ባለሙዎቹ አመላክተዋል፡፡
ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!