
👉ጥንቃቄ፦
ባሕር ዳር: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ያለደንበኛ ፈቃድ ገንዘብ የሚያስተላልፈው መተግበሪያ
👉በአደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ነው።
👉 መተግበሪያው ያለደንበኛው ፈቃድ ገንዘብ ያስተላልፋል።
ደምበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy የሚሰኝ መተግበሪያ መኾኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳውቋል።
ባንኩ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ ነው።
ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መኾኑን ጠቁሟል።
መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ ያስተላልፋል ተብሏል።
ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ማለቱን ኢትዮጵያ ፕሬስ አስነብቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!