
ባሕር ዳር: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ እና የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሕዝባዊ የሰላም ውይይት ተካሂዷል።
የሰላም ውይይቱን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የራያ ቆቦ ወረዳ እና የቆቦ ከተማ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች መርተውታል።
በውይይቱ የመንግሥት የሰላምና ልማት አቅጣጫዎች ተነስተዋል። ከራያ ቆቦ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የአካባቢው ሰላም በዘላቂነት በሚረጋገጥበት ሁኔታ ውይይት ተደርጓል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!