
ባሕር ዳር: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ሕዝባዊ የሰላም ውይይት ተካሂዷል።
በከተማ አሥተዳደሩ በአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ የጸጉር አዲኮ ቀበሌ እና በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የደብረታቦር ኢየሱስ ቀበሌ አሥተዳደር ነዋሪዎች ጋር ነው የሰላም ውይይት የተካሄደው። ውይይቱ ”ለሰላም ግንባታ የኅብረተሰብ ሚና” በሚል መሪ መልዕክት መካሄዱን ከደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ሕዝባዊ የሰላም ውይይቱ ማኅበረሰቡ የሰላሙ ባለቤት እንዲኾን እና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የልማት ሥራዎች እንዲሠሩ ለማድረግ ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!