በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ከኮሶበር ቻግኒ መስመር የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል።

30

ባሕር ዳር: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

ከኮሶበር ፣ ቻግኒ በተዘረጋው 66 ኪሎ ቮልት ኃይል አስተላለፊ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ቻግኒን ጨምሮ በመተከል ዞን፣ በግልገል በለስ ከተማ፣ በማንዱራ፣ በፖዌ፣ በዲባጠ፣ በቡለን፣ በደብረ ዘይት፣ በዳንጉርና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል ብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባስተላለፈው መልዕክት በኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ የተፈጠረው ብልሽት ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን ብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለዘላቂ ሰላም መስፈን ኅብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡
Next articleስለይቅርታ ሕጉ ምን ይላል?