
ባሕር ዳር: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተሳተፉበት የአፍሪካ ኢነርጂ ጉባዔ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም እየተካሄደ ነው።
ጉባዔውን የታንዛኒያ መንግሥት፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ በጋራ እንዳዘጋጁት ተመላክቷል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ዓለም ባንክ በቀጣይ አምስት ዓመታት ለ300 ሚሊዮን አፍሪካዊያን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ የያዙት ውጥን እውን እንዲኾ ያለመ ጉባዔ ነው መባሉን ኢቢሲ ዘገቧል።
አህጉሪቱ ያላትን እምቅ የታዳሽ ኃይል ወደ ሥራ ለማስገባት ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑም ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!