የሳይበር ስጋቶችን መከላከል ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት ወሳኝ እንደሆነ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

38

ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞና ውጥኖች ላይ ያተኮረ ኤግዚቢሽን እና ዓውደ ጥናት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው ። መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ከባቢን መገንባት እና የሳይበር ስጋቶችን መከላከል ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት ወሳኝ ነው ብለዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የመጨረሻው የትግበራ አመት ላይ እንገኛለን ያሉት አቶ ተመስገን ፤ በስትራቴጂው የባለፉት የትግበራ ጊዜያት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ ሲሆን በአንጻሩም የተለያዩ ተግዳሮቶች መግጠማቸውን ተናግረዋል። ይህንንም መነሻ በማድረግ የቀጣይ 5 አመታት “የዲጂታል ኢትዮጰያ 20230 ስትራቴጂ” መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመድረኩ ላይ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስኬት ወሳኝ የሆኑ ሁለት ረቂቅ ስትራቴጂዎች ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ እነዚህም: “የዲጂታል መንግስት ስትራቴጂ” እና “የኤሌክትሮኒክ ንግድ ስትራቴጂ” ናቸው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ሥምምነት ከከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ተፈራረመ።
Next articleአሕጉር አቀፍ የእንስሳት ጤና ጉባኤ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።