
ባሕር ዳር: ጥር 19/2017 ዓ.ም( አሚኮ) በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ናይሮቢ የገቡት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በቤተ መንግሥት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ኅብረት ተቋማዊ ማሻሻያ ስብሰባ በኬኒያ ናይሮቢ እየተካሄደ ነው። በስብሰባውም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች ተሳትፈዋል።
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በ2016 ዓ.ም የአፍሪካ ኅብረት የተቋማዊ ማሻሻያ ሥራ እንዲመሩ የተመረጡ መሪ ናቸው።
ኢቢሲ እንደዘገበው በናይሮቢ ቤተ መንግሥት እየተደረገ ያለው ስብሰባ በማሻሻያ ሥራ ሂደት እና ቀጣይነት ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ነው ተብሏል።
ኅብረቱ በማሻሻያ ሥራው ተቋማዊ መዋቅር፣ የገንዘብ ምንጭ፣ የተቋሙ ትኩረት እና ውጤታማነት ላይ መፍትሔ ለመስጠት ያለመ እንደኾነም ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!