
አዲስ አበባ: ጥር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የብልጽግና ፓርቲ ከጥር 23 እስከ ጥር 25 በአድዋ ሙዚየም የሚያካሄደውን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ጉባኤው የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አካል የሚሳተፍበት በመኾኑ እና በሥስት ወሳኝ ምክንያቶች ጉባኤው ተጠባቂ ነው ብለዋል
አንደኛው ብልጽግና ትልቅ ሕዝብ እና ሀገር የሚመራ ፓርቲ በመኾኑ የፓርቲው ውሳኔዎች ትልቅ እንደሚኾን መታመኑ፣ ሁለተኛው ፓርቲው 15 ነጥብ 7 ሚሊዮን አባላት ያሉት ትልቅ ፓርቲ መኾኑ፣ ሶስተኛው ፓርቲው ሀገሪቱን አፍሪካዊት የብልጽግና ማማ እንደሚያደርግ ስለሚጠበቅ እና ባለፉት ዓመታት 7 ነጥብ 2 በመቶ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ ያደረገ ፓርቲ በመሆኑ ጉባኤው ተጠባቂ አድርጎታል ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንቱ
እንደምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለፃ ፓርቲው ባለፉት አመታት የኑሮ ውድነትን ከማቃለል ምርትን ከማሳደግ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ከመፈፀም በጎ ፈቃድ እንዲያድግ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ዘርፍ እድገት ማምጣቱ እና በዲፕሊማሲ ዜጋ ተኮር እና ወዳጅ የሚያበዛ አካሔድን የሚከተል ፓርቲ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ብልጽግና በጉባኤው ከቃል እስከ ባህል የሚል መልዕክት ቃል የመረጠ ሲሆን ይህም የሀገሪቱ እድገት ህብረተሰቡን በባለቤትነት እንዲይዘው የሚያደርግ ፓርቲው እስከአሁን የሰራውን እና ወደፊት የሚሰራውን ዘላቂ የህብረተሰብ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያሳይ በመሆኑ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
የፓርቲው የጉባኤ ዝግጅት ቀደም ብሎ በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲከናወን መቆየቱን ያነሱት አቶ አደም የዶክመንት እና የሎጀስቲክስ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነው የጉባኤው መጀመር ብቻ እየተጠበቀ ነው ብለዋል። በጉባኤው 1700 ተሳታፊዎች በድምፅ የሚሳተፉ ሲሆን ያለድምፅ በተሳትፎ የሚካፈሉ ተጋባዦችም እንዳሉ አንስተዋል።
ይህም በአንድኛው ጉባኤ የተሳተፉ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚቴ አባላት፣ በየደረጃው ተመርጠው የመጡ የፓርቲው አባለት በድምፅ እና ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም ከውጭ ሀገራት ከ15 እህት ፓርቲዎች የተጋበዙ ይሳተፋሉ። ከጉባኤው የሚጠበቁ ውሳኔዎችን ሲያብራሩ 3 ትልልቅ ውሳኔዎችን ፓርቲው እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል ብለዋል።
አንደኛ ፓርቲውን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎች ሲሆኑ እነዚህም-በአሰራር
-በመመሪያ እና
– በእሳቤ ናቸው
ሁለተኛው መንግስትን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎች ሲሆኑ
-የተቋም ግንባታ
-ዘላቂ ሰላም
-ኢኮኖሚያዊ አቅምን መጠቀም
-ስራ ፈጠራን ኑሮ ውድነትን
_በማህበራዊ ዘርፍ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ትልልቅ ውሳኔዎችን ያሳልፋል
ሶስተኛው የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር ውሳኔዎች ሲሆን
-የዜጋ እና የሀገረ ክብር መጠበቅ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ፓርቲው ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
ፓርቲው በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ለሚሰራው ስራ ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!