ስደተኞችን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው።

22

ደባርቅ: ጥር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍሪካ ቀንድ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት የአማራ ክልል ማሥተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አሥተባባሪዎች እና የዳባት ወረዳ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ፕሮጀክቱ በደባት ያስገነባቸውን እና በግንባታ ላይ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

የሰው ልጆች በተለያዩ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች የትውልድ ሀገራቸውን ጥለው ይሰደዳሉ።

ስደተኞቹ በሰፈሩበት አካባቢ ሊኖር የሚችለውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ከሚሠሩ ፕሮጀክቶች መካከል ደግሞ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት አንዱ ነው።

በአፍሪካ ቀንድ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት የአማራ ክልል ማሥተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አሥተባባሪ መንግሥቱ ድልነሳ ፕሮጀክቱ የውጭ ስደተኞችን የሚያስጠልሉ ሀገራትን መሠረት አድርጎ የሚሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

በዳባት ወረዳ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን ታሳቢ በማድረግ በወረዳው የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን ተናግረዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በመንገድ፣ በንፁህ መጠጥ ውኃ፣ በግብርና፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፎች ከ40 በላይ የልማት ሥራዎችን እያከናዎኑ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።
ፕሮጀክቱ፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገቢያ ትስስር እና ገብያ ማረጋጋት መርሐ ግብር መሳተፉንም አመላክተዋል።

በነጋዴዎች እና በእንግዳ ተቀባዩ ማኅበረሰብ መካከል የሚኖረውን የባሕል ልዩነት በማጥበብ የጋራ መግባባት እንዲኖር ለማድረግ ማኅበራዊ አውድን በመፍጠር እየሠራ ነው ብለዋል።

የዳባት ወረዳ ምክትል አሥተዳዳሪ መርሻ ወረታ ፕሮጀክቱ በወረዳው በ2015 ዓ.ም ሥራ መጀመሩን አንስተዋል።

በተለያዩ ዘርፎች ማኅበረሰቡን በማገልገል ውጤታማ ሥራ እየሠራ የመጣ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

የፕሮጀክቱ አሥተባባሪዎች፣ የወረዳው መሪዎች፣ በመጠለያ የሚገኙ ስደተኞች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ በልማት ሥራው ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል።

ማኅበረሰቡ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን እንዲደግፍ እና እንዲጠብቅም ፈጥሪ አቅርበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጅማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ ልንከተላቸው ይጋባሉ ያሏቸው ነጥቦች:-
Next articleባለፉት ወራት ከ597 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ተስቧል።