
ባሕርዳር: ጥር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጅማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ ልንከተላቸው የሚገቡ ዐሥር አቅጣጫዎች ብለው አስቀምጠዋል።
1. ቡናን በጥራትና በስፋት ማምረት፤ በተለይ የጥሪኝ ቡና ስፔሻሊቲን ማስፋፋት።
2. ልዩ ልዩ ኦርጋኒክ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን በልዩ ብራንድ ጅማ ላይ ማቀነባበር።
3. የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረትና በመጠቀም፣ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን ማምረት፣ ማሸግና መላክ።
4. የከብት ወተትና ሥጋ፤ እንዲሁም የዶሮ ዕንቁላል እና ሥጋን በጥራትና በብዛት በማምረት አሽጎ መላክ።
5. ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ በሚመጥን መልኩ ማቀነባበር፣ ማሸግና መላክ።
6. ልዩ ልዩ የእንጨት ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በፋብሪካዎች በጥራት ማምረት።
7. የሸክላ ፋብሪዎችን በማስፋፋት፤ ለወለል፣ ለግድግዳ እና ለጣራ የሚያገለግሉ የግንባታ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ።
8. የጅማንና የአካባቢዋን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ጸጋዎችን በማልማትና በማስተሣሠር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ።
9. የጅማ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅበትን ሰላሙን እና እንግዳ ተቀባይነቱን ማጽናት።
10. ጎጂ ማኅበራዊ ልማዶችን እና ደካማ የሥራ ባሕልን ማሻሻል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!