
ባሕርዳር: ጥር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ በነገ ልዩ ስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የሥድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያዳምጣል ተብሏል። ሁለት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ ያጸድቃል ነው የተባለው።
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ፣ የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!