የፍትሕ ተቋማት የመንግሥትን እና የሕዝብን ጥቅም ማስከበር ይጠበቅባቸዋል።

26

ደብረ ብርሃን: ጥር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ በጀት ዓመቱን የመደበኛ እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም የፍትሕ አካላት በተገኙበት ግምገማዊ የውይይት መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም የፍትሕ ተቋማት የመንግሥትን እና የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር መሥራት ዋና ተግባራቸዉ ሊኾን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በክልሉ በተፈጠረዉ የሰላም እጦት ሳቢያ በሕግ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ላይ የመርማሪ ቡድን በማዋቀር እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ያለአግባብ የመንግሥትን ሀብትን ያባከኑ እና የሕዝብ ጥቅምን የተጋፉ አካላት ላይም በሕግ ተጠያቂ እንዲኾኑ የማድረግ ሥራ መሠራቱንም አንስተዋል፡፡

ለአብነት በሕገወጥ መንገድ በቤት ማኅበር በደላሎች የተደራጁ እና መሬት ያለአግባብ በጥቅም አሳልፈዉ የሰጡ አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ መወሰዱን ጠቅሰዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጽናትን እና ብርታትን እንማር” ብፁዕ አቡነ አብርሃም
Next articleየመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በቡርቃ የተሃድሶ ማዕከል ስልጠና የወሰዱ ታጣቂዎች ተመረቁ።