
ባሕር ዳር: ጥር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰባር አጽሙ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል በድምቀት ተከብሮ በሰላም ተጠናቅቋል። በዓሉ ከዋዜማው ጀምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ተከብሯል።
በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ሊቃውንት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ በምዕመናን በተገኙበት ነው በድምቀት የተከበረው።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ የጣና ሐይቅን በማረክ ወደ መንበረ ክብሩ ተመልሷል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም በድምቀት የተከበረውን በዓል በቀጥታ ሥርጭት ላስተላለፈው አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ምስጋና አቅርበዋል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ክብረ በዓላትን በቀጥታ ሥርጭት ለሕዝብ የሚያደርስ፣ ለባሕል፣ ለታሪክ እና ለእሴት መጠበቅ በትኩረት የሚሠራ ታላቅ ተቋም ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!