የሰባር ጊዮርጊሥ ክብረ በዓል በባሕር ዳር በድምቀት ተጀምሯል።

35

ባሕር ዳር: ጥር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰባር አጽሙ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊሥ ካቴድራል በማለዳው በድምቀት ተጀምሯል።
የባሕር ዳር እና አካባቢው የተሰባሰቡ ምዕመናን በፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊሥ ካቴድራል ዙሪያ ታድመዋል።
የተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎችን ሲፈጽሙ ያደሩት ሊቃውንት እና ካህናት ታቦተ ሕጉን ከቤተ ክርስቲያን በማውጣት ላይ ይገኛሉ።
ታቦተ ሕጉም በምዕመናን እልልታ እና ሆታ፣ በካህናት ወረብ እና ሽብሸባ ታጅቦ በጣና ሐይቅ ዳርቻ ወደተዘጋጀለት ቦታ ይጓዛል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ24 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአጋሮ እና በሻሻ የልማት ሥራዎች ጎብኝተዋል።