
ባሕርዳር: ጥር 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሊባኖስ እና በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 359 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሷል።
በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እንደቀጠለ ነው። በሳምንቱ 156 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። በሳዑዲ ዓረቢያ የነበሩ 203 ኢትዮጵያውያንም ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያ፣ በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራም እየተሠራ መኾኑም ተመላክቷል።
ከሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሚያዚያ 04/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ሥራ እስካሁን 90 ሺህ 101 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
