ረቂቅ አዋጁ የመሬት አሥተዳደር እና አጠቃቀምን በማዘመን ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

61

ጎንደር: ጥር 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የገጠር መሬት አሥተዳደር እና አጠቃቀም ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የግብዓት ማሠባሠቢያ መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው። ረቂቅ አዋጁ ያሉ ጉድለቶችን በመሙላት የመሬት አሥተዳደር እና አጠቃቀምን በማዘመን ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የግብዓት ማሠባሠቢያ መድረኩ በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ እና ጎንደር እየተካሄደ መኾኑን የክልሉ መሬት ቢሮ ምክትል ኀላፊ አዳነ መሐሪ (ዶ.ር) ገልጸዋል። ረቂቅ አዋጁ ከሚመለከታቸው አካላት ግብዓት ከተሠበሠበ በኀላ ሲጸድቅ የመሬትን አሥተዳደር እና አጠቃቀም በማዘመን ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ምክትል ቢሮ ኀላፊው ጠቅሰዋል።

በተለይ የወል መሬትን በአግባቡ ለማሥተዳደር እና የሴቶች፣ የሕጻናት፣ የአካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን መብት እና ጥቅም ለማስከበር ከባለፈው አዋጅ በበለጠ አሁን ውይይት ላይ ያለው ረቂቅ አዋጅ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በምክክር መድረኩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ገንቢ ሃሳብ እየሠጡ ሲኾን ረቂቁን ለማጠናከር እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ አገኘሁ አበባው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጤናማ የሕይዎት ዘይቤን በመከተል እና መደበኛ የጤና ክትትል በማድረግ የጀርባ ሕመምን መከላከል ይገባል፡፡
Next articleየስንዴ ምርታማነት በምግብ ራስን ከመቻልም በላይ ነው።