
ደብረ ብርሃን: ጥር 16/2017 ዓ.ም(አሚኮ) በዘንድሮዉ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ በነባር 599 እና በአዲስ 846 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ። በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች የተራቆቱ ቦታዎችን ማልማት በመቻላችን ተጠቃሚ ኾነናል ይላሉ።
ተፈጥሮን በመጠበቅ የአፈር ለምነቱን መመለስ እንደቻሉም አንስተዋል። በአትክልት እና ፍራፍሬ እና በእንስሳት ልማት ዉጤታማ ሥራ እንድንሠራ መሰረት ኾኖናል ብለዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ መርሻ አይሳነው በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራው ለውጥ በማምጣት በተለይም ለወጣቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸዉ አድርጓል ነው ያሉት።
በቀጣይም ባለሙያዎችን በማሠልጠን፣ አርሶ አደሩን የሥራው አካል እና ባለቤት በማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ ነው የገለጹት። “የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ለኾነ አካል ብቻ የሚተው ባለመኾኑ” በትብብር በመሥራት ተፈጥሮን ወደ ነበረበት መመለስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
