
ባሕርዳር: ጥር 16/2017 ዓ.ም( አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢቲ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ” በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀን ሥራ አስጀምረናል። ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ እድል የፈጠረ ነው” ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
