
ፍኖተ ሰላም: ጥር 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወር አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ ሥራዎች መድረክ በፍኖተ ሰላም ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው ባለፉት ስድስት ወራት የጤና ባለሙያው በችግር ውስጥም ኾኖ የሙያውን መርሕ በመጠበቅ ማኅበረሰቡን እያገለገለ መኾኑን ገልጸዋል።
የማኅበረሰቡን የጤና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል አኹንም በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ነው አቶ ሙላት የተናገሩት። በግምገማ መድረኩ ላይ የሁሉም ወረዳ የጤና ተቋማት ባለሙያዎች እና ኀላፊዎች እንዲኹም የጤና ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
በመድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት በጤናው ዘርፍ የታዩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች ተገምግመው በቀጣይ ሥራዎች ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
