
ባሕር ዳር: ጥር 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀነሲ የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የወሰዱ ሠራተኞችን አስመርቋል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ የኾነውን የቴክኖሎጂና የዲጂታል ዘርፍ ተዋናይ ለመኾን የ5 ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ሚናው የላቀ መኾኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለምታደርገው የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም ያለው፣ የበቃ፣ በክህሎት የዳበረ፣ ሁሉንም መሸከም የሚችል የቴክኖሎጂ ዕውቀትን የታጠቀ ዜጋ ማፍራት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ይሄን ማድረግ ከቻልን የምንፈልገውን ውጤት በአጭር ጊዜ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።
በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ለማሳካት ሰፊ ሥራዎች በመሥራት መሠረት ተጥሏል ያሉት ሚኒስትሩ ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተዘጋጀውን የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ሥልጠና እድል መጠቀም ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ በዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች ራስን በማስታጠቅ ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ የሥራ እድሎችን መጋራት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
