የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ በእንስሳት ሃብት ልማት የተሻለ ውጤት እንዲገኝ እያደረገ መኾኑን አርሶ አደሮች ተናገሩ።

17

ጎንደር: ጥር 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል። የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ አበራ አደባ በተያዘው የበጋ ወቅት የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ በ18 ተፋሰሶች ላይ ለመሥራት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል ።

የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራው ለተከታታይ ሰላሳ የሥራ ቀናት የሚከወን መኾኑን የገለጹት ኀላፊው ከ10 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተሳታፊ እንደሚኾኑም ተናግረዋል። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት በጎንደር ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ መኮነን የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ለሌማት ትሩፋት ሥራ፣ ለመስኖ እና ሌሎችም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መኾኑን አንስተዋል።

በመርሐ ግብሩ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት በተሠሩ የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራዎች የመስኖ ልማት ተጠቃሚ እንዲኾኑና ምርትና ምርታመነት እንዲያድግ ማድረጉን ገልጸዋል። በእንስሳት ሃብት ሥራ ላይ የተሻለ ውጤት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራን ለማስቀጠል ዝግጁ መኾናቸውንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ቃልኪዳን ኃይሌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካን ዕድገት በትክክለኛው መንገድ ለመምራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የጎላ ነው።
Next articleምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ ።