የተፋሰስ ልማት ሥራ በሰብል ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን አርሶ አደሮች ተናገሩ።

31

እንጅባራ: ጥር 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች፣ ፈረሰኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ዃሻይ ተፋሰስ ላይ ተጀምሯል።

የቀበሌው አርሶ አደሮችም ሰላማችንን እየጠበቅን ልማታችንን እናስቀጥላለን ብለዋል። ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በሠሩት የተፋሰስ ልማት ሥራ በሰብል ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውንም አርሶ አደሮቹ አንስተዋል።

የለሙ ተፋሰሶችን ከንክኪ ነፃ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አርሶ አደሮቹ ገልጸዋል። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የተገኙት የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና መሬት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉጌታ ምህረት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ የኅብረተሰቡ የኑሮ መሠረት ኾኖ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የለሙ ተፋሰሶች የአካባቢው ገፅታን ከማሻሻል ባሻገር ለወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ አዎንታዊ ሚናቸውን እየተወጡ እንደኾነም ገልጸዋል።

የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አድማሱ ጌታሁን በከተማ አሥተዳደሩ በ8 ቀበሌዎች 13 ተፋሰሶችን ለማልማት የሚያስችል አልሚ የሰው ኀይል ልየታ፣ የቅየሳ እና ሌሎችም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀው ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ የደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለክልል የደም ባንኮች ድጋፍ አደረገ።
Next articleየአፍሪካን ዕድገት በትክክለኛው መንገድ ለመምራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የጎላ ነው።