የተፈጥሮ ሃብት ልማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክሮ እንደሚከናወን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገለጸ።

32

ሰቆጣ: ጥር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የግብር መምሪያ አዘጋጅነት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዳግም ባይነሳኝ የተፈጥሮ ሃብት ልማትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ አጠናክረን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል። በዋግ ኽምራ የሚከሰተውን ድርቅ መከላከል የሚቻለው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን በዘመናዊ መንገድ ማልማት ሲቻል እንደኾነም አስገንዝበዋል።

በንቅናቄ መድረኩ የተገኙት አቶ ተሾመ ስመኝ እስከዛሬ በለሙ ተፋሰሶች ላይ ጅምር ለውጦች ቢኖሩም በቀጣይ ዘመናዊ አሠራርን በመከተል ሁሉም ማኅበረሰብ የተፈጥሮ ሃብትን ለመጠበቅ በጋራ እንደሚጥሩ ገልጸዋል። ሌሎች ሃሳብ የሰጡ ተሳታፊዎችም ከሪፖርት ያለፈ ተግባር ለማከናወን በጋራ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከ369 በላይ ተፋሰሶች ያሉ ሲኾነ ከእነዚህም ውስጥ 9 ተፋሰሶች በአዲስ የሚጀምሩ መኾኑን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ሞገስ ኀይሌ ገልጸዋል። የተፈጥሮ ሃብት ልማት ባለፉት ዓመታት በማልማታችን ጅምር ለውጦች ቢኖርም ከዚህ የበለጠ ለውጥ ለማምጣት ለዋግ ሕዝብ አማራጭ የሌለው ተግባር መኾኑንም ኀላፊው ተናግረዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ከጥር 20 ጀምሮ በንቅናቄ የሚጀመር ሲሆን ለ25 ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል።

ዘጋቢ: ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተደራሽነት ያሳየውን ዕድገት ያክል ሀገር በቀል ዕውቀትን ከዘመናዊ ትምህርት ለማዋሐድም ይሠራል” አስራት አጸደወይን (ዶ.ር)
Next articleየኢትዮጵያ የደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለክልል የደም ባንኮች ድጋፍ አደረገ።