በአንደኛው ዙር የመስኖ ልማት ከ32 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

29

ባሕር ዳር: ጥር 14/2017 ዓ.ም(አሚኮ) በአማራ ክልል በአንደኛ ዙር የበጋ መስኖ ልማት 342 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን የግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡ ክልሉ ወንዞችን ጨምሮ ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል እምቅ ሃብት ያለው ክልል ነው፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት እንደ ክልል በአንደኛ ዙር የመስኖ ልማት 342 ሺህ 480 ሄክታር መሬት ለማልማት አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን በግብርና ቢሮ የመስኖ ሰብል ልማት ባለሙያ አስማረ መንግስቱ ተናግረዋል፡፡

ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ስነ ምህዳርን ያገናዘበ፣ የሃብት አጠቃቀምን እና ውጤታማነትን የበለጠ ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት እየተሠሩ ነው ብለዋል። በተመረጡ ሰብሎች ላይም ዕቅድ በማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት እና የተግባር ሥራዎች ሲተገበሩ መቆየታቸውንም ገልጸዋል።

ከታቀደው ውስጥም 299 ሺህ 888 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ነው ያሉት ባለሙያው፡፡ የመስኖ ልማት ተግባራቱ ከባለፈው ዓመት የምርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር የተሻለ አፈጻጸም እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ በአንደኛው ዙር የመስኖ ልማት 32 ሚሊዮን 128 ሺህ 763 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ባለሙያው ተናግረዋል።፡

የክልሉን የመስኖ ልማት ለማሳደግ የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች እና አሠራሮች ተግባር ላይ እየዋሉ ነውም ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከኅብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ በመሥራት በትምህርት ላይ የተፈጠረውን ችግር እንደሚፈታ የትምህርት ቢሮ ገለጸ።
Next articleበተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ ለማሳ እርከን ሥራ ሰፊ ትኩረት ይሰጣል።