በሰሜን ወሎ ዞን በዓይና ቡግና ወረዳ ለተቸገሩ ወገኖች የዕለት የምግብ ድጋፍ ተደረገ።

146

ወልድያ: ጥር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ድጋፉን ያደረገው ኢማጅን ዋን ደይ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። የኢማጅን ዋን ደይ የአማራ ክልል ኘሮጀት አስተባባሪ ከሰተ አድማስ ድርጅቱ በትምህርት እና ሕጻናት ጥበቃ ላይ ይሠራል ብለዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ለመደገፍ ከ800 ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ዱቄት እና ማካሮኒ ለዞኑ ምግብ ዋስትና እና አደጋ መከላከል አስረክበዋል።

ከዕለት ምግብ ድጋፍ በተጨማሪ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አለሙ ይመር ድጋፉ ለማኅበረሰቡ በቀጥታ እንዲደርስ ጽሕፈት ቤቱ ተረክቦ ወደ ዓይና ቡግና ወረዳ ሸኝቷል ብለዋል።

የድርጅቱ አስተባባሪ ከሰተ አድማስ ኢማጅን ዋን ደይ ድጋፉን ከቦታው ድረስ በመውሰድ ለሕዝቡ እንደሚያሰራጭም ነግረውናል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ያገኘችውን ሀገራዊ ምክክር የማድረግ ዕድል ሁሉም አካላት በአግባቡ መጠቀም ይገባቸዋል” ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር)
Next articleብልጽግና ፓርቲ ለመተግበር ቃል የገባቸው ጉዳዮች በአግባቡ እየተተገበሩ መኾናቸውን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።