የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳትን ጎበኙ።

81

ጎንደር: ጥር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርስቲ የምሥረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው። በዓሉ ከጥር 14/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ 20 በሚኾኑ ሁነቶች ይከበራል።

በዩኒቨርስቲው የምስረታ በዓል ላይ ለመሳተፍ ጎንደር ከተማ የገቡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ.ር) ጨምሮ የመንግሥት ሥራ ኀላፊዎች፣ የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ማምጣት አሁንም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገለጸ።
Next article“ኢትዮጵያ ያገኘችውን ሀገራዊ ምክክር የማድረግ ዕድል ሁሉም አካላት በአግባቡ መጠቀም ይገባቸዋል” ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር)