
ባሕር ዳር: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ 1 ሺህ 950 ቶን የዓሣ ምርት መገኘቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ዳይሬክተር ሃይሉ ይርጋ ባለፉት 6 ወራት የዓሣ ሃብት ልማትን ለማስፋፋት በትኩረት ተሰርቷል ብለዋል።
በተለይም በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሚከናወነውን የዓሣ ሃብት ልማት ለማጠናከር በትብብር እየተሠራ መኾኑን ተናግርዋል። እስካሁን በግድቡ 74 ማኅበራት ተደራጅተው ዕውቅና እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ከእነዚህ መካከል 28 ማኅበራት ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
ማኅበራቱ በዓሣ ማስገሪያ መረብ እና በዓሳ ምግብ አሠራር እንዲኹም ዓሳ የማስገር ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚያስችል ተግባር ተኮረ ሥልጠና መሰጠቱን ኤፍቢሲ አስነብቧል። ለዓሳ ማስገሪያ የሚውሉ 29 ጀልባዎች እና 1 ሺህ 400 መረቦችን ማቅረብ መቻሉን ጠቁመው፣ በግማሽ ዓመቱ ከሕዳሴ ግድብ 1 ሺህ 947 ቶን የዓሳ ምርት ማምረት መቻሉን አስረድተዋል።
የዓሳ ምርቱ 12 ፍሪጅ በተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች አማካኝነት ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ መኾኑንም አብራርተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
