
አዲስ አበባ: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና አባላት በመቄዶንያ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል። በዕለቱም የምሳ ግብዣ እና የተለያዩ አልባሳት፣ ዘይት፣ የማብሰያ ዕቃዎች እና የምግብ እህል ነው ድጋፍ የተደረገው።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በጉብኝታቸው የተመለከቱት ነገር እጅግ እንዳስገረማቸው እና በማዕከሉ እየተሠራ ያለው የሰብዓዊነት ተግባር ትልቅ መኾኑን ገልጸዋል።
ወደፊት በገቢ ማሰባሰብም ኾነ በሌላ ድጋፍ ሠራዊቱ በግልም ኾነ በቡድን እንደ ተቋም ከመቄዶኒያ ጎን ነው ብለዋል። ሌሎች ተቋማትም መቄዶንያንን እንዲጎበኙ እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የማኅበሩ መሥራች ቢኒያም በለጠ ለተደረገው ድጋፍ በአረጋውያኑ እና በማኅበሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በማኅበሩ እንክብካቤ እየተደረገላቸው የሚገኙ አረጋውያን ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ: ቤቴል መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
