ጅቡቲ ወደብ የደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓጓዘ መኾኑ ተገለጸ።

81

ባሕር ዳር: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዩሪያ እና ዳፕ ማዳበሪያ የጫኑ ስድሰት መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸው ተገልጿል።

እስከአሁን በወደቡ ከደረሰው 313 ሺህ 260 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 256 ሺህ 398 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን የሚኾነው ወደ ኢትዮጵያ መላኩም ተመላክቷል። ቀሪው ማዳበሪያ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

56 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች ሰባተኛ መርከብ ጥር 12/2017 ዓ.ም ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ደርሳ ጭነት እያራገፈች ነው ተብሏል።

በሚቀጥሉት ቀናትም ተጨማሪ አራት የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በጅቡቲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሥራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል” የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል
Next article” ኢትዮጵያ ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሠራች ነው” በለጠ ሞላ (ዶ.ር)